ስምም
ዘርፍ(Area of specialization): General
English equivalent: system
ዝርዝር በአማርኛ፤ እንደአንድ አካል ተስማምተው የሚሰሩ ንኡስ አካላት ስብስብ
English description:
ትርጉም፤ አዲስ ሳይንስ
የስያሜው መነሻ፤ የእንግሊዝኛው ቃል “እንደአንድ አካል ተስማምተው የሚሰሩ የንኡስ አካላት ስብስብ” ለማለት የቀረበ ትርጉም አለው። የቃሉም ድምጸት ለእንግሊዝኛው ቅርበት ስላለው ተስተዋሽነቱንና ከዚህም ተያይዞ ተቀባይነቱን ይጨምርለታል የሚል ግምት በመያዙ ጭምር ይህ ትርጉም ተሠንዝሯል።
የዚህ ትርጉም ትችት፤
ነባር ትርጉም፤ ስርአት
የነባር ትርጉም ምንጭ፤ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዴሚ የሳይንስና ቴክሎጂ መዝገበ-ቃላት
የነባር ትርጉም ትችት፤ ብዛት ባላቸው ዘርፎችና ቢያንስ ለሁለት ፅንሰ-ሐሣቦች ጥቅም ላይ የዋለ፤ ሆኖም በጣም ጠቃሚ ቃል ነው።
ማስገንዘቢያ፤ "መሠንዘር" (እዚህ ከተጠቀሰ)፡ ሃሳብ እንደማቅረብ ይቆጠር።