ጤና | Health


ከዜና ምንጮቻችን... | From our sources


ዛሬ | Today...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |

ትናንት | Yesterday...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |

ባለፉት ሰባት ቀናት | During the last seven days (dates in brackets)...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |
አጫጭር ዜናዎችና የዜና ትርጉሞች

እጅግ ደቂቅ ኤሌክትረመካኒክ ስምሞች፣ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት፣ ጣልቃ-ገብነትና ሕክምና

በዛሬው ዕለት ሮይተርስ የNature'ን መፅሔት ጠቅሶ እንዳስነበበን፤ Nano electro-mechanical systems (NEMS) ወይም (ትርጉም ብንሠነዝር) "እጅግ ደቂቅ ኤሌክትረመካኒካዊ ስምሞች " ተብለው የሚጠሩ ኣጓጓዦችን በደም-ሥር በኩል ለሕክምና የተሰናዳ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት (rhibonucleic acid, RNA) በመጫንና ወደካንሰር ዕጢዎች በመላክ ማከም ይቻል መሆኑን በፓሳዴና የሚገኘው የካሊፎርኒያ የቴክኖሎጂ ተቋም (California Institute of Technology) ተመራማሪዎች መሞከራቸውንና ኣበረታች ውጤት ማየታቸውን ዘግበዋል።

ለመሆኑ እነዚህ ጥቃቅን ቁሶች ምንድን ናቸው? እንዴትስ ይፈበረካሉ? ይህ ዘርፍ ሰፊ መድብለ-ዕውቀት (multi-disciplinary) ከመሆኑም በላይ ከሚፈበረኩት እካላት መጠን ማነስ (ደቃቃነት) የተነሳ የራሱ የሆኑ የረቀቁ የምርምርና የበሳል እውቀት ክምችት ያለው ነው። ለመንደርደሪያ ያህል ግን የሚከተለውን ለማለት እንሞክራለን። እነዚህ ስምሞች፤ ኤሌክትሪካዊና መካኒካዊ ( እንዳስፈላጊነቱ እንደኤለክትሪክ ሞተር ያሉ እካላትን፣ ልክ እንደእስክሪፕቶ ላስቲክና የወረቀት ቁራጭ (ይህንን ምሳሌ፤ ተማሪዎች ሳለን ሁላችንም የሞከርነው ስለሆነ ለማለት ነው) በኤሌክትሪክ (ትርፍና ጉድለት ይዘት) ምክንያት የሚሳሳቡ ወይም የሚገፋፉ እካላትን፣ ደጋፊና ተሸካሚ ኣካላትን፣ የእሽክርክሪት ማስተላለፊያ ኣካላትን (gears, shafts,etc.) እና/ወይም ሌሎችን እካላት) የያዙ እካላት ናቸው። ኣፈበራረካቸው ከመጠናቸው ማነስ የተነሳ፤ በተለምዶኣዊዉ በስልና ጠንካራ ብረት በመቁረጥ (milling, shaping, lathing, etc) ሳይሆን፤ ባብዛኛው እንደኤሌክትሮኒክ ወጥ-ግጥምጥም እካላት (integrated circuits, IC) በእንግሊዝኛው "photolithography" ወይም ከተለያዪ ንጥረ-ነገሮች በተሰሩ ንብርብር ቁሶች ላይ የተለያዩ ቅርፆችን በብርሃንና በሸፋኝ ንጥረ-ነገሮች (photoresist chemicals) በመለያየትና በእሲዶች በመሸርሸር፣ ወይም ደግሞ በኤሌክትሮን ውርጅብኝ (electron beam) እማካኝነት ያልተፈለጉ ክፍሎችን በማትነን ቀሪውን በመቅረጽ ነው። በቅርቡ እየተሞከረ የሚገኘው ዘዴ ደግሞ፤ ራሳቸውን በተወሰኑ ቅርፆች በሚደረድሩ ሞለኪዩሎች በመጠቀም የታቀዱ ቅርጻቅርጾችን በመፈብረክና እነዚህን በመገጣጠም ነው። በሁለተኛው ዘዴ የሚፈበረኩት እጅግ ደቂቅ ኤሌክተረመካኒካዊ ስምሞች ከላይ በተጠቀሰው ዘዴ ከሚፈበረኩት በመጠን ያነሱ፤ ሆኖም ግን ቅርጻቸውንና መጠናቸውን እንደላይኞቹ እንደተፈለገው ለመቆጣጠር የሚያዳግቱ ናቸው።

የሕክምናው ዘዴ የረቀቀ ቢሆንም፤ በጥቂት ቃላትና ጥልቀት ባነሰው ኣገላለጽ ከዚህ በታች ከብዙ በጥቂቱ ለማለት እንሞክራለን። ሕክምናው መሠረት ያደረገው rhibonucleotide reductase የተሰኘውንና የካንሰርን ዕጢ ለማደግ የሚያስችለው ኤንዛይም እንዲመረት ወሳኝነት ያለውን የዘር ባህርይ (gene) ሥራ ማስቆምን ነው። ይህ የዘር ባህርይ ሥራውን እንዳይሠራ ለማድረግ ተመራማሪዎቹ የተጠቀሙበት ዘዴ ከካንሰሩ ዕጢ ድረስ "ኣናሳ ጣልቃ-ገብ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት" (small interfering rhibonucleic acid, siRNAs) በመላክና የካንሰር ሕዋሶች (cells) ከላይ የተጠቀሰውን ኤንዛይም እንዳያመርቱ ጣልቃ በመግባት (በመረበሽ) ነው። በርግጥ ይህ ዘዴ እንድ ተጨማሪና ዋና ሊባል የሚችለው ገጽታው የካንሰር ሕዋሶችን ለይቶ ማግኘትና "በጥባጩ" ጣልቃ-ገብ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት ከነዚህ ህዋሶች ስስ ሽፋን ዘልቆ መግባት እንዲችል ክዚያም የታቀደለትን ተግባር እንዲፈጽም ማድረግ ነው።

የሕክምናውን ዘዴ ፍቱንነት ካሁኑ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም፤ ተመራማሪዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ የምርምር መርኃ-ግብራቸው ሙከራ ከተደረገላቸው የተለያዩ የካንሰር ሕሙማን መካከል የቆዳ ካንሰር ሕሙማን በሆኑት በሶስቱ በተደረገው የዕጢ ምርመራ ጣልቃ-ገቡ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት እንደታለመው ከካንሰር ሕዋሶች መግባት መቻሉን ይህም ጥናቱ ሊመረምራቸው ከተነሳባቸው መላ-ምቶች ቢያንስ ሁለቱ መሳካታቸውን፡ እነዚህም እጅግ ረቂቅ ኤሌክተረመካሚክ ስምሞችን ተጠቅሞ በደም ሥር በኩል ፈዋሽ "ጭነቶችን" መላክ እንደሚቻል፣ በተጨማሪም የተላከው ጣልቃ-ገቡ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት ከታለመለት የካንሰር ሕዋሶች ዘልቆ መግባት መቻሉን ማረጋገጥ እንደሆነ ተዘግቧል።


ከኢንፍሉዌንዛ - A (የአሳማ ጉንፋን፤ Swine flu) የተያያዙ ጠቋሚዎች

በአስጊ ሁኔታ እየተስፋፋ የሚገኘዉንና እንደጎርጎርዮሳዊው ቀመር እስከ April 30 2009 ድረስ የአሳማ ጉንፋን (“Swine flu”)፤ ከዚያም ወዲህ በይፋዊ ስያሜ ኢንፍሉዌንዛ-A (ወይም H1N1)፤ የተባለዉን በሽታ በተመለከተ ከዓለም የጤና ድርጅት (WHO)ና ከዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (Centers for Disease Control and Prevention) እንዲሁም ከሌሎች አካላት የተሰባሰቡ ጠቋሚዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። ለዕለት-ተዕለት ዜናዎች በስተቀኝ የሚገኘዉን ንዑስ ገጽ ይመልከቱ።

ጠቋሚዎች፤

| 2ተዛማጅ አርእስት አግኝተዋል። |

የተለያዩ፤ | Miscellaneous


እንዲሁም በምርምር ለተሰማራችሁ፤