ሳይንስና ማህበረሰብ | Science and Society


ከዜና ምንጮቻችን... | From our sources


ዛሬ | Today...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |

ትናንት | Yesterday...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |

ባለፉት ሰባት ቀናት | During the last seven days (dates in brackets)...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |
አጫጭር ዜናዎችና የዜና ትርጉሞች | Brief reports

ስውር መብራት አጥፊ እጆች?

የብሪታንያ የዜና ስርጭት ድርጅት (BBC) እንደዘገበው፤ የዩናይትድ እስቴትስ ማዕከላዊ የኤክትሪክ ሃይል ማሰራጫ (grid) መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ስምም (system) “በውጭ ሰላዮች" ተገብቶበት ነበር። ይህ “አገባብ” በኢንተርኔት በኩል ሲሆን የሁለት ሃያላን ሀገራት ስም፤ ማለትም የሩስያና የቻይና፤ በዘገባው ተጠቅሷል።

በዚሁ ዘገባ ላይ መጠይቅ በተደረገላቸው የኢንተርኔት መረጃ ደህንነት (security) ባለሙያዎች እንደተባለው፤ ይህ እርምጃ ምናልባት ለወደፊት ሊከሰት በሚችል ግጭት ወቅት ኤኮኖሚያዊ ጉዳት ለማድረስና የሃይል ሚዛንን ለመለወጥ ዓላማ ሊውል የሚችል ተግባር ነበር። የዚህም አተገባበር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እነዚህን መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ከሩቅ በማዘዝ የኤሌክትሪክ ሃይል ፍሰትን በማቋረጥ እንደሆነ እምነታቸውን ገልጸዋል።

ባሁኑ ዘመን የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የግለሰቦች ኮምፒዩተሮች ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ በመሆናቸው የተነሳ የረቀቁ አሳሳች የኮምፒዩተር ፕሮግራሞችንና መልእክቶችን በመጠቀም ያልተፈቀደላቸው አካላት በነዚህ ስምሞች እየገቡ የተከማቹ መረጃዎችን በመኮረጅ፤ ቁልፍ ቃላትን (passwords) እና የመልዕክት ልውውጦችን ጆሮ በመጥባት (eavesdropping)፣ እነዚህን የኮምፒዩተር ስምሞች በመቆጣጠር ሌሎችን የኮምፒዩተር ስምሞች በመሰለል ወይም ሳይጠሩት-አቤት ኢሜይል (spam) መላኪያነት በመጠቀም፣ ወይም ለሌላ ላልተፈቀደ ተግባር በማዋል ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ።

በተጨማሪም፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉ (hijacked) ኮምፒዩተሮችን በአካል ሳይሆን በመረጃ ልውውጥ ረገድ እርስ በርስ በማገናኘና አዲስ የኮምፒዩተር መረብ (network) (የሰለባዎች/የምርኮኞች መረብ (botnet)) በማዋቀር ሳይጠሩት-አቤት ኢ-ሜይል ከመላኪያነት በተጨማሪ ሌሎችን መረቦች ለማጨናነቂያነት (denial of service attack) መጠቀሚያ በማድረግ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በሀገራችንስ ተመሳሳይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል በምን ያህል ደረጃ ጥንቃቄ እየተደረገ ይሆን?

| አንድ ተዛማጅ ርእስ አግኝተዋል። |

ማስገንዘቢያ Disclaimer: