በየቀኑ በአማካይ አራት ጊዜ የሚከለሱትን የዕለት-ተዕለት የሳይንስ፣ የጤና፣ የቴክኖሎጂ፣ የግብርናና ሥነ-ምግብ፣ የተፈጥሮ ኣካባቢ፣ ወዘተርፈ ዜናዎች ለማንበብ በስተግራ ከሚገኘው ዝርዝር የመረጡትን ይጠቁሙ።
Please click on menu items on the left to view classified science and technology news updated four times a day. Place pointer over menu items to view title of topic.

ቴክኖሎጂ | Technology


ከዜና ምንጮቻችን... | From our sources


ዛሬ | Today...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |

ትናንት | Yesterday...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |

ባለፉት ሰባት ቀናት | During the last seven days (dates in brackets)...

| ዕለተ ዐርብ፡ ፰/፮/፳፻፲፩፤ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ከ፭ ደቂቃ የተከለሰ | Updated on 15/02/2019 at 21:05 GMT |
አጫጭር ዜናዎችና የዜና ትርጉሞች | Brief reports

እጅግ ደቂቅ ኤሌክትረመካኒክ ስምሞች፣ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት፣ ጣልቃ-ገብነትና ሕክምና

በዛሬው ዕለት ሮይተርስ የNature'ን መፅሔት ጠቅሶ እንዳስነበበን፤ Nano electro-mechanical systems (NEMS) ወይም (ትርጉም ብንሠነዝር) "እጅግ ደቂቅ ኤሌክትረመካኒካዊ ስምሞች " ተብለው የሚጠሩ ኣጓጓዦችን በደም-ሥር በኩል ለሕክምና የተሰናዳ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት (rhibonucleic acid, RNA) በመጫንና ወደካንሰር ዕጢዎች በመላክ ማከም ይቻል መሆኑን በፓሳዴና የሚገኘው የካሊፎርኒያ የቴክኖሎጂ ተቋም (California Institute of Technology) ተመራማሪዎች መሞከራቸውንና ኣበረታች ውጤት ማየታቸውን ዘግበዋል።

ለመሆኑ እነዚህ ጥቃቅን ቁሶች ምንድን ናቸው? እንዴትስ ይፈበረካሉ? ይህ ዘርፍ ሰፊ መድብለ-ዕውቀት (multi-disciplinary) ከመሆኑም በላይ ከሚፈበረኩት እካላት መጠን ማነስ (ደቃቃነት) የተነሳ የራሱ የሆኑ የረቀቁ የምርምርና የበሳል እውቀት ክምችት ያለው ነው። ለመንደርደሪያ ያህል ግን የሚከተለውን ለማለት እንሞክራለን። እነዚህ ስምሞች፤ ኤሌክትሪካዊና መካኒካዊ ( እንዳስፈላጊነቱ እንደኤለክትሪክ ሞተር ያሉ እካላትን፣ ልክ እንደእስክሪፕቶ ላስቲክና የወረቀት ቁራጭ (ይህንን ምሳሌ፤ ተማሪዎች ሳለን ሁላችንም የሞከርነው ስለሆነ ለማለት ነው) በኤሌክትሪክ (ትርፍና ጉድለት ይዘት) ምክንያት የሚሳሳቡ ወይም የሚገፋፉ እካላትን፣ ደጋፊና ተሸካሚ ኣካላትን፣ የእሽክርክሪት ማስተላለፊያ ኣካላትን (gears, shafts,etc.) እና/ወይም ሌሎችን እካላት) የያዙ እካላት ናቸው። ኣፈበራረካቸው ከመጠናቸው ማነስ የተነሳ፤ በተለምዶኣዊዉ በስልና ጠንካራ ብረት በመቁረጥ (milling, shaping, lathing, etc) ሳይሆን፤ ባብዛኛው እንደኤሌክትሮኒክ ወጥ-ግጥምጥም እካላት (integrated circuits, IC) በእንግሊዝኛው "photolithography" ወይም ከተለያዪ ንጥረ-ነገሮች በተሰሩ ንብርብር ቁሶች ላይ የተለያዩ ቅርፆችን በብርሃንና በሸፋኝ ንጥረ-ነገሮች (photoresist chemicals) በመለያየትና በእሲዶች በመሸርሸር፣ ወይም ደግሞ በኤሌክትሮን ውርጅብኝ (electron beam) እማካኝነት ያልተፈለጉ ክፍሎችን በማትነን ቀሪውን በመቅረጽ ነው። በቅርቡ እየተሞከረ የሚገኘው ዘዴ ደግሞ፤ ራሳቸውን በተወሰኑ ቅርፆች በሚደረድሩ ሞለኪዩሎች በመጠቀም የታቀዱ ቅርጻቅርጾችን በመፈብረክና እነዚህን በመገጣጠም ነው። በሁለተኛው ዘዴ የሚፈበረኩት እጅግ ደቂቅ ኤሌክተረመካኒካዊ ስምሞች ከላይ በተጠቀሰው ዘዴ ከሚፈበረኩት በመጠን ያነሱ፤ ሆኖም ግን ቅርጻቸውንና መጠናቸውን እንደላይኞቹ እንደተፈለገው ለመቆጣጠር የሚያዳግቱ ናቸው።

የሕክምናው ዘዴ የረቀቀ ቢሆንም፤ በጥቂት ቃላትና ጥልቀት ባነሰው ኣገላለጽ ከዚህ በታች ከብዙ በጥቂቱ ለማለት እንሞክራለን። ሕክምናው መሠረት ያደረገው rhibonucleotide reductase የተሰኘውንና የካንሰርን ዕጢ ለማደግ የሚያስችለው ኤንዛይም እንዲመረት ወሳኝነት ያለውን የዘር ባህርይ (gene) ሥራ ማስቆምን ነው። ይህ የዘር ባህርይ ሥራውን እንዳይሠራ ለማድረግ ተመራማሪዎቹ የተጠቀሙበት ዘዴ ከካንሰሩ ዕጢ ድረስ "ኣናሳ ጣልቃ-ገብ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት" (small interfering rhibonucleic acid, siRNAs) በመላክና የካንሰር ሕዋሶች (cells) ከላይ የተጠቀሰውን ኤንዛይም እንዳያመርቱ ጣልቃ በመግባት (በመረበሽ) ነው። በርግጥ ይህ ዘዴ እንድ ተጨማሪና ዋና ሊባል የሚችለው ገጽታው የካንሰር ሕዋሶችን ለይቶ ማግኘትና "በጥባጩ" ጣልቃ-ገብ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት ከነዚህ ህዋሶች ስስ ሽፋን ዘልቆ መግባት እንዲችል ክዚያም የታቀደለትን ተግባር እንዲፈጽም ማድረግ ነው።

የሕክምናውን ዘዴ ፍቱንነት ካሁኑ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም፤ ተመራማሪዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ የምርምር መርኃ-ግብራቸው ሙከራ ከተደረገላቸው የተለያዩ የካንሰር ሕሙማን መካከል የቆዳ ካንሰር ሕሙማን በሆኑት በሶስቱ በተደረገው የዕጢ ምርመራ ጣልቃ-ገቡ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት እንደታለመው ከካንሰር ሕዋሶች መግባት መቻሉን ይህም ጥናቱ ሊመረምራቸው ከተነሳባቸው መላ-ምቶች ቢያንስ ሁለቱ መሳካታቸውን፡ እነዚህም እጅግ ረቂቅ ኤሌክተረመካሚክ ስምሞችን ተጠቅሞ በደም ሥር በኩል ፈዋሽ "ጭነቶችን" መላክ እንደሚቻል፣ በተጨማሪም የተላከው ጣልቃ-ገቡ ገሚስ-ኀብለ-ሕይወት ከታለመለት የካንሰር ሕዋሶች ዘልቆ መግባት መቻሉን ማረጋገጥ እንደሆነ ተዘግቧል።


ስውር መብራት አጥፊ እጆች?

የብሪታንያ የዜና ስርጭት ድርጅት (BBC) እንደዘገበው፤ የዩናይትድ እስቴትስ ማዕከላዊ የኤክትሪክ ሃይል ማሰራጫ (grid) መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ስምም (system) “በውጭ ሰላዮች" ተገብቶበት ነበር። ይህ “አገባብ” በኢንተርኔት በኩል ሲሆን የሁለት ሃያላን ሀገራት ስም፤ ማለትም የሩስያና የቻይና፤ በዘገባው ተጠቅሷል።

በዚሁ ዘገባ ላይ መጠይቅ በተደረገላቸው የኢንተርኔት መረጃ ደህንነት (security) ባለሙያዎች እንደተባለው፤ ይህ እርምጃ ምናልባት ለወደፊት ሊከሰት በሚችል ግጭት ወቅት ኤኮኖሚያዊ ጉዳት ለማድረስና የሃይል ሚዛንን ለመለወጥ ዓላማ ሊውል የሚችል ተግባር ነበር። የዚህም አተገባበር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እነዚህን መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ከሩቅ በማዘዝ የኤሌክትሪክ ሃይል ፍሰትን በማቋረጥ እንደሆነ እምነታቸውን ገልጸዋል።

ባሁኑ ዘመን የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የግለሰቦች ኮምፒዩተሮች ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ በመሆናቸው የተነሳ የረቀቁ አሳሳች የኮምፒዩተር ፕሮግራሞችንና መልእክቶችን በመጠቀም ያልተፈቀደላቸው አካላት በነዚህ ስምሞች እየገቡ የተከማቹ መረጃዎችን በመኮረጅ፤ ቁልፍ ቃላትን (passwords) እና የመልዕክት ልውውጦችን ጆሮ በመጥባት (eavesdropping)፣ እነዚህን የኮምፒዩተር ስምሞች በመቆጣጠር ሌሎችን የኮምፒዩተር ስምሞች በመሰለል ወይም ሳይጠሩት-አቤት ኢሜይል (spam) መላኪያነት በመጠቀም፣ ወይም ለሌላ ላልተፈቀደ ተግባር በማዋል ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ።

በተጨማሪም፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉ (hijacked) ኮምፒዩተሮችን በአካል ሳይሆን በመረጃ ልውውጥ ረገድ እርስ በርስ በማገናኘና አዲስ የኮምፒዩተር መረብ (network) (የሰለባዎች/የምርኮኞች መረብ (botnet)) በማዋቀር ሳይጠሩት-አቤት ኢ-ሜይል ከመላኪያነት በተጨማሪ ሌሎችን መረቦች ለማጨናነቂያነት (denial of service attack) መጠቀሚያ በማድረግ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በሀገራችንስ ተመሳሳይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል በምን ያህል ደረጃ ጥንቃቄ እየተደረገ ይሆን?


ላንድሳት-5 ("Landsat-5") 25ኛ አመት እድሜዋን "አከበረች"።

"Landsat" በመባል የሚታወቀው የዩናይትድ ስቴትስ የምርምር መርሃ፥ግብር ወደጠፈር እስካሁን ካመጠቃቸው ጭፍራዎች (satellites) አንዷ የሆነችውና ለሶስት አመታት እድሜ ብቻ ተገምታ የተሰራችው "Landsat 5" ከመጠቀችበት ከየካቲት 22 1977 (ወይም እ.ኤ.አ March 1፣ 1984) አንስታ ላለፉት 25 አመታት ግልጋሎት እየሰጠች ትገኛለች። በርግጥም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አንድ ባለሥልጣን እንዳሉት፤ ይህ ሰኬት " የምህንድስናው ጥራትና ከምህንድስናው ጀርባ ያሉት ወንዶችና ሴቶች ታታሪነት ፍሬ ነው"::

የላንድሳት መርሃ-ግብር በዩናይትድ ስቴትስ የአየርና የጠፈር ባለሥልጣን (ናሳ)ና በ ዩናይትድ ስቴትስ የሥነ-ምድር መረጃ ሰብሳቢ ድርጅት (ዩ.ኤስ. ጂኦሎጂካል ሰርቬይ) በጋራ የሚመራ ሲሆን ላለፉት ከ30 ዓመታት በላይ የዓለማችንን ገጽታ በተለያዩ “ንጥር” ቀለማት (spectra) ዲጂታል ምስል በጭፍሮቹ አማካይነት በመቅረጽና በመቆጣጠሪያ ጣቢያዎቹ በመቀበል ምድርን ከሩቅ የመከታተልና የማጥናትን ጥበብ (Remote sensing) ለማዳበር ከፍተኛ ድርሻውን የተወጣ ነው። በዚህ መርሃ-ግብር አህጉሮችን፣ የባህር ጠረፎቻቸውንና አካባቢዎቻቸዉን ላለፉት 3 አሠርት-ዓመታት በመከታተል በዓለማችን ላይ የደረሱትን ሰው-ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ለውጦች ለመከታተል ተችሏል።

ላንድሳት-5 በየ99 ደቂቃው አንድ ጊዜና፤ እስካሁን ድረስ ደግሞ ከ130 ሺህ በላይ ጊዜ አለማችንን ዙራታለች። ምንም እንኳ የምስል መሰብሰቢያ አካሏ የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ ክፍል ችግር ቢኖርበት፤ ለሚቀጥሉት 3 አመታት ተጨማሪ ግልጋሎት እንደምትሰጥ ይጠበቃል። በተመሳሳይ ጊዜም የመርሃ፥ግብሩ ተከታይ ጭፍራ ሊተካት ዝግጁ እንደሚሆን ይጠበቃል።

አጠቃላዩን የ"Landsat" ተከታታይ ጭፍሮች ዝርዝር በሌላ ቀጣይ ዘገባ የምንመለስበት ይሆናል።

| 3ተዛማጅ አርእስት አግኝተዋል። |

ማስገንዘቢያ Disclaimer: